ዳንኤል 2:34, 35 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 አንተም አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቅቃቸው አየህ።+ 35 በዚህ ጊዜ ብረቱ፣ ሸክላው፣ መዳቡ፣ ብሩና ወርቁ ሁሉም በአንድነት ተሰባበሩ፤ በበጋ ወቅት በአውድማ ላይ እንደሚቀር ገለባም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራርጎ ወሰዳቸው። ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ትልቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ።
34 አንተም አንድ ድንጋይ የሰው እጅ ሳይነካው ተፈንቅሎ ከብረትና ከሸክላ የተሠሩትን የምስሉን እግሮች ሲመታቸውና ሲያደቅቃቸው አየህ።+ 35 በዚህ ጊዜ ብረቱ፣ ሸክላው፣ መዳቡ፣ ብሩና ወርቁ ሁሉም በአንድነት ተሰባበሩ፤ በበጋ ወቅት በአውድማ ላይ እንደሚቀር ገለባም ሆኑ፤ ነፋስም አንዳች ሳያስቀር ጠራርጎ ወሰዳቸው። ምስሉን የመታው ድንጋይ ግን ትልቅ ተራራ ሆነ፤ ምድርንም ሁሉ ሞላ።