17 በልብህም ‘ይህን ሀብት ያፈራሁት በራሴ ኃይልና በእጄ ብርታት ነው’+ ብለህ ብታስብ 18 ሀብት እንድታፈራ ኃይል የሰጠህ አምላክህ ይሖዋ መሆኑን አስታውስ፤+ ይህን ያደረገው ዛሬ እንደሆነው ሁሉ ለአባቶችህ በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ለመፈጸም ነው።+
19 “አምላክህን ይሖዋን ብትረሳና ሌሎች አማልክትን ብትከተል እንዲሁም እነሱን ብታገለግልና ለእነሱ ብትሰግድ፣ በእርግጥ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ እመሠክርባችኋለሁ።+