የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘዳግም 6:10-12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “አምላክህ ይሖዋ ለአንተ ለመስጠት ለአባቶችህ ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ወደማለላቸው ምድር+ ሲያስገባህና በዚያም አንተ ያልገነባሃቸውን ታላላቅና ያማሩ ከተሞች፣+ 11 አንተ ባልደከምክባቸው የተለያዩ መልካም ነገሮች የተሞሉ ቤቶችን፣ አንተ ያልቦረቦርካቸውን የውኃ ማጠራቀሚያዎች እንዲሁም አንተ ያልተከልካቸውን የወይን ተክሎችና የወይራ ዛፎች ስታገኝ፣ በልተህም ስትጠግብ+ 12 ከግብፅ ምድር ከባርነት ቤት ያወጣህን ይሖዋን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ።+

  • ዘዳግም 8:12-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በልተህ ስትጠግብ፣ ጥሩ ጥሩ ቤቶችን ሠርተህ በዚያ መኖር ስትጀምር፣+ 13 ከብትህና መንጋህ ሲበዛ፣ ብርህና ወርቅህ ሲበራከት እንዲሁም የአንተ የሆነው ሁሉ እየበዛ ሲሄድ 14 ልብህ እንዳይታበይና+ ከግብፅ ምድር ይኸውም ከባርነት ቤት ያወጣህን አምላክህን ይሖዋን እንዳያስረሳህ ተጠንቀቅ፤+

  • ዘዳግም 32:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 የሹሩን* ሲወፍር በዓመፀኝነት ተራገጠ።

      ሰባህ፤ ፈረጠምክ፤ ደለብክ።+

      ስለሆነም የሠራውን አምላክ ተወ፤+

      አዳኝ የሆነለትን ዓለት ናቀ።

  • ዘዳግም 32:18
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 18 አባት የሆነህን ዓለት ረሳኸው፤+

      የወለደህንም አምላክ አላስታወስክም።+

  • ኢሳይያስ 17:10
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 አንቺ፣* አዳኝ አምላክሽን ረስተሻልና፤+

      መሸሸጊያ ዓለትሽንም+ አላስታወስሽም።

      ያማሩ ተክሎችን ያለማሽውና

      በመካከሉም የባዕድ* ቡቃያ የተከልሽው ለዚህ ነው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ