ኢዩኤል 2:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 ታላቁና የሚያስፈራው የይሖዋ ቀን+ ከመምጣቱ በፊትፀሐይ ወደ ጨለማ፣ ጨረቃም ወደ ደም ይለወጣሉ።+ ማቴዎስ 24:29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 29 “በእነዚያ ቀናት ከሚኖረው መከራ በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤+ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይላትም ይናወጣሉ።+ ሉቃስ 21:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 “እንዲሁም በፀሐይ፣ በጨረቃና በከዋክብት ላይ ምልክቶች ይታያሉ፤+ በምድርም ላይ ሕዝቦች ከባሕሩ ድምፅና ነውጥ የተነሳ የሚያደርጉት ጠፍቷቸው ይጨነቃሉ። ራእይ 9:2 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 2 የጥልቁንም መግቢያ ከፈተው፤ በመግቢያውም በኩል ከታላቅ እቶን እንደሚወጣ ጭስ ያለ ጭስ ወጣ፤ ከዚያ በወጣው ጭስም ፀሐይ ጨለመች፤+ አየሩም ጠቆረ።
29 “በእነዚያ ቀናት ከሚኖረው መከራ በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤+ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይላትም ይናወጣሉ።+