16 ከዚህ ይልቅ ይህ የሆነው በነቢዩ ኢዩኤል በኩል እንዲህ ተብሎ በተነገረው መሠረት ነው፦ 17 ‘አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመጨረሻው ቀን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ ወንዶች ልጆቻችሁና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ፤ ወጣቶቻችሁ ራእዮችን ያያሉ፤ ሽማግሌዎቻችሁም ሕልም ያልማሉ፤+ 18 በዚያ ቀን በወንዶች ባሪያዎቼና በሴቶች ባሪያዎቼ ላይ ሳይቀር ከመንፈሴ አፈሳለሁ፤ እነሱም ትንቢት ይናገራሉ።+