ኢዮብ 36:27, 28 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 27 እሱ የውኃ ጠብታዎችን ወደ ላይ ይስባል፤+ጭጋጉም ወደ ዝናብነት ይለወጣል፤28 ከዚያም ደመናት ያዘንባሉ፤+በሰው ልጆችም ላይ ዶፍ ያወርዳሉ። መክብብ 1:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 ጅረቶች* ሁሉ ወደ ባሕር ይፈስሳሉ፤ ሆኖም ባሕሩ አይሞላም።+ ጅረቶቹ እንደገና ይፈስሱ ዘንድ ወደሚነሱበት ወደዚያው ቦታ ተመልሰው ይሄዳሉ።+