42 በዚህ ጊዜ አምላክ ፊቱን ከእነሱ አዞረ፤ በነቢያትም መጻሕፍት እንዲህ ተብሎ በተጻፈው መሠረት የሰማይ ሠራዊትን እንዲያመልኩ ተዋቸው፦+ ‘የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ለ40 ዓመት በምድረ በዳ መባና መሥዋዕት ያቀረባችሁት ለእኔ ነበር? 43 ይልቁንም ልታመልኳቸው የሠራችኋቸውን ምስሎች ይኸውም የሞሎክን+ ድንኳንና ሮምፋ የሚባለውን አምላክ ኮከብ ተሸክማችሁ ተጓዛችሁ። ስለዚህ ከባቢሎን ወዲያ እንድትሰደዱ አደርጋችኋለሁ።’+