ኢሳይያስ 62:8, 9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+ 9 ሆኖም እህሉን፣ የሚሰበስቡት ሰዎች ይበሉታል፤ ይሖዋንም ያወድሳሉ፤ወይኑንም፣ የሚለቅሙት ሰዎች ቅዱስ በሆኑት ቅጥር ግቢዎቼ ውስጥ ይጠጡታል።”+ ሚክያስ 4:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 እያንዳንዱም ከወይኑና ከበለስ ዛፉ ሥር ይቀመጣል፤*+የሚያስፈራቸውም አይኖርም፤+የሠራዊት ጌታ የይሖዋ አፍ ተናግሯልና።
8 ይሖዋ በቀኝ እጁ፣ ብርቱ በሆነውም ክንዱ እንዲህ ሲል ምሏል፦ “ከእንግዲህ እህልሽን ለጠላቶችሽ መብል እንዲሆን አልሰጥም፤የደከምሽበትንም አዲስ የወይን ጠጅ የባዕድ አገር ሰዎች አይጠጡትም።+ 9 ሆኖም እህሉን፣ የሚሰበስቡት ሰዎች ይበሉታል፤ ይሖዋንም ያወድሳሉ፤ወይኑንም፣ የሚለቅሙት ሰዎች ቅዱስ በሆኑት ቅጥር ግቢዎቼ ውስጥ ይጠጡታል።”+