መሳፍንት 11:12, 13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 ከዚያም ዮፍታሔ ለአሞናውያን+ ንጉሥ “ምድሬን ልትወጋ የመጣኸው ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው?”* ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞች ላከ። 13 የአሞናውያን ንጉሥም የዮፍታሔን መልእክተኞች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ያደረግኩት እስራኤል ከግብፅ በወጣበት ጊዜ ከአርኖን+ አንስቶ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ+ ድረስ ያለውን መሬቴን ስለወሰደብኝ ነው።+ አሁንም መሬቴን በሰላም መልሱልኝ።” ኤርምያስ 49:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 49 ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም? ወራሽስ የለውም? ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+ ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”
12 ከዚያም ዮፍታሔ ለአሞናውያን+ ንጉሥ “ምድሬን ልትወጋ የመጣኸው ከእኔ ጋር ምን ጠብ ቢኖርህ ነው?”* ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞች ላከ። 13 የአሞናውያን ንጉሥም የዮፍታሔን መልእክተኞች እንዲህ አላቸው፦ “ይህን ያደረግኩት እስራኤል ከግብፅ በወጣበት ጊዜ ከአርኖን+ አንስቶ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ+ ድረስ ያለውን መሬቴን ስለወሰደብኝ ነው።+ አሁንም መሬቴን በሰላም መልሱልኝ።”
49 ይሖዋ፣ ስለ አሞናውያን+ እንዲህ ይላል፦ “እስራኤል ወንዶች ልጆች የሉትም? ወራሽስ የለውም? ታዲያ ማልካም፣+ ጋድን የወረሰው ለምንድን ነው?+ ሕዝቦቹስ በእስራኤል ከተሞች ውስጥ የሚኖሩት ለምንድን ነው?”