የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • 1 ሳሙኤል 12:15
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 15 ሆኖም የይሖዋን ቃል ባትታዘዙና በይሖዋ ትእዛዝ ላይ ብታምፁ የይሖዋ እጅ በእናንተና በአባቶቻችሁ ላይ ይሆናል።+

  • 1 ዜና መዋዕል 28:9
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 9 “አንተም ልጄ ሰለሞን ሆይ፣ የአባትህን አምላክ እወቅ፤ በሙሉ ልብና*+ በደስተኛ* ነፍስ* አገልግለው፤ ይሖዋ ልብን ሁሉ ይመረምራልና፤+ ሐሳብንና ውስጣዊ ዝንባሌን ሁሉ ይረዳል።+ ብትፈልገው ይገኝልሃል፤+ ከተውከው ግን ለዘላለም ይተውሃል።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:17
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 17 ስለዚህ የከለዳውያንን+ ንጉሥ አመጣባቸው፤ እሱም ወጣቶቻቸውን በቤተ መቅደሳቸው+ ውስጥ በሰይፍ ገደለ፤+ ለወጣቱም ሆነ ለድንግሊቱ፣ ለሽማግሌውም ሆነ ለአቅመ ደካማው አልራራም።+ አምላክ ሁሉንም በእጁ አሳልፎ ሰጠው።+

  • 2 ዜና መዋዕል 36:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 የእውነተኛውን አምላክ ቤት አቃጠለ፤+ የኢየሩሳሌምን ቅጥር አፈረሰ፤+ የማይደፈሩ ማማዎቿን ሁሉ በእሳት አቃጠለ፤ እንዲሁም ውድ የሆኑትን ዕቃዎች በሙሉ አወደመ።+

  • ኤርምያስ 17:27
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 27 “‘“የሰንበትን ቀን ሳትቀድሱ፣ በሰንበት ቀን ሸክም ተሸክማችሁ በኢየሩሳሌም በሮች በመግባት ትእዛዜን ብትጥሱ፣ በሮቿን በእሳት አነዳለሁ፤ እሳቱም የኢየሩሳሌምን የማይደፈሩ ማማዎች ይበላል፤+ ፈጽሞም አይጠፋም።”’”+

  • ኤርምያስ 37:8
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 8 ከለዳውያኑም ተመልሰው መጥተው ይህችን ከተማ ይወጓታል፤ ይይዟታልም፤ በእሳትም ያቃጥሏታል።”+

  • ኤርምያስ 52:12-14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 12 በአምስተኛው ወር፣ ከወሩም በአሥረኛው ቀን ይኸውም ንጉሥ ናቡከደነጾር* በነገሠ በ19ኛው ዓመት፣ የዘቦች አለቃና የባቢሎን ንጉሥ አገልጋይ የሆነው ናቡዛራዳን ወደ ኢየሩሳሌም መጣ።+ 13 እሱም የይሖዋን ቤት፣ የንጉሡን ቤትና* በኢየሩሳሌም የሚገኙ ቤቶችን በሙሉ አቃጠለ፤+ ትላልቅ ቤቶችንም ሁሉ በእሳት አጋየ። 14 ከዘቦቹ አለቃ ጋር የነበረው የከለዳውያን ሠራዊት በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያለውን ቅጥር በሙሉ አፈረሰ።+

  • ሆሴዕ 8:14
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 14 እስራኤል ፈጣሪውን ረስቷል፤+ ቤተ መቅደሶችንም ገንብቷል፤+

      ይሁዳም የተመሸጉ ከተሞችን አብዝቷል።+

      እኔ ግን በከተሞቹ ላይ እሳት እሰዳለሁ፤

      እሳቱም የእያንዳንዳቸውን ማማዎች ይበላል።”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ