-
ዘኁልቁ 6:3, 4አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 ስእለት የተሳለው ሰው ከወይን ጠጅና ከሚያሰክር ሌላ መጠጥ መራቅ ይኖርበታል። የወይን ጠጅ ኮምጣጤ ወይም የማንኛውም ዓይነት የሚያሰክር መጠጥ ኮምጣጤ አይጠጣ።+ ከወይን ፍሬ የተዘጋጀን ማንኛውንም መጠጥ አይጠጣ፤ የወይን ፍሬም ሆነ ዘቢብ አይብላ። 4 ናዝራዊ ሆኖ በሚቆይበት ጊዜ ሁሉ ከወይን ተክል የተዘጋጀን ማንኛውንም ነገር፣ ያልበሰለውን የወይን ፍሬም ሆነ ግልፋፊውን ፈጽሞ መብላት የለበትም።
-