-
2 ነገሥት 23:15, 16አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
15 በቤቴል የነበረውንም መሠዊያ ይኸውም እስራኤላውያን ኃጢአት እንዲሠሩ ያደረገው የናባጥ ልጅ ኢዮርብዓም የሠራውን ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ አፈረሰ።+ ያን መሠዊያና ከፍ ያለ የማምለኪያ ቦታ ካፈረሰ በኋላ ቦታውን አቃጠለው፤ ፈጭቶም አመድ አደረገው፤ የማምለኪያ ግንዱንም* አቃጠለ።+
16 ኢዮስያስ ዞር ብሎ በተራራው ላይ ያሉትን መቃብሮች ባየ ጊዜ አፅሞቹን ከመቃብሮቹ ውስጥ አስወጥቶ በመሠዊያው ላይ በማቃጠል እነዚህ ነገሮች እንደሚሆኑ አስቀድሞ የተናገረው የእውነተኛው አምላክ ሰው ባወጀው የይሖዋ ቃል መሠረት መሠዊያውን አረከሰ።+
-
-
ሆሴዕ 10:2አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
መሠዊያዎቻቸውን የሚሰባብር፣ ዓምዶቻቸውንም የሚያፈራርስ አለ።
-