ኢሳይያስ 7:8 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 8 የሶርያ ራስ ደማስቆ፣የደማስቆ ራስ ደግሞ ረጺን ነውና። ኤፍሬም በ65 ዓመት ውስጥብትንትኑ ወጥቶ ሕዝብ መሆኑ ይቀራል።+ ኢሳይያስ 8:4 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 4 ልጁ ‘አባዬ!’ እና ‘እማዬ!’ ብሎ መጥራት ከመቻሉ በፊት የደማስቆ ሀብትና የሰማርያ ምርኮ በአሦር ንጉሥ ፊት ይወሰዳል።”+ ኢሳይያስ 17:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 17 በደማስቆ ላይ የተላለፈ ፍርድ፦+ “እነሆ፣ ደማስቆ ከተማ መሆኗ ይቀራል፤የፍርስራሽ ክምርም ትሆናለች።+