14 ከይሖዋ የመጣ አንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤
በብሔራት መካከል አንድ መልእክተኛ ተልኳል፦
“በአንድነት ተሰብሰቡ፤ በእሷም ላይ ውጡ፤
ለጦርነት ተዘጋጁ።”+
15 “እነሆ፣ በብሔራት መካከል ከቁብ የማትቆጠር፣
በሰዎችም መካከል የተናቅክ አድርጌሃለሁና።+
16 አንተ በቋጥኝ መሸሸጊያ ውስጥ የምትኖር፣
በጣም ረጅሙን ኮረብታ የያዝክ ሆይ፣
የነዛኸው ሽብርና
የልብህ እብሪት አታሎሃል።
ጎጆህን እንደ ንስር በከፍታ ቦታ ላይ ብትሠራም፣
እኔ ከዚያ አወርድሃለሁ” ይላል ይሖዋ።