የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ዘፍጥረት 27:41, 42
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 41 ይሁን እንጂ ኤሳው አባቱ ያዕቆብን ስለባረከው ለያዕቆብ ከፍተኛ ጥላቻ አደረበት።+ ኤሳውም በልቡ “ለአባቴ ሐዘን የምንቀመጥበት ቀን ሩቅ አይደለም።+ ከዚያ በኋላ ወንድሜን ያዕቆብን እገድለዋለሁ” ይል ነበር። 42 ርብቃ ታላቁ ልጇ ኤሳው ያለው ነገር ሲነገራት ወዲያውኑ ለታናሹ ልጇ ለያዕቆብ እንዲህ የሚል መልእክት ላከችበት፦ “ወንድምህ ኤሳው አንተን በመግደል ሊበቀልህ እያሰበ ነው።*

  • ዘኁልቁ 20:20, 21
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 እሱ ግን አሁንም “በዚህ ማለፍ አትችልም”+ ሲል መልስ ሰጠ። ከዚያም ኤዶም ብዙ ሕዝብና ኃያል ሠራዊት* ይዞ ሊገጥመው ወጣ። 21 በዚህ መንገድ ኤዶም እስራኤል በክልሉ እንዳያልፍ ከለከለ፤ ስለዚህ እስራኤል ከእሱ ተመለሰ።+

  • መዝሙር 83:4-6
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  4 “የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣

      ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ።+

       5 የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤*

      በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤*+

       6 የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና+ አጋራውያን፣+

  • መዝሙር 137:7
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    •  7 ይሖዋ ሆይ፣ ኢየሩሳሌም በወደቀችበት ቀን

      ኤዶማውያን ያሉትን አስታውስ፤

      “አፍርሷት! ከሥረ መሠረቷ አፍርሷት!”+ ብለው ነበር።

  • ኢዩኤል 3:19
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 19 ግብፅ ግን ባድማ ትሆናለች፤+

      ኤዶምም በምድራቸው ንጹሕ ደም በማፍሰስ+

      በይሁዳ ሕዝብ ላይ ግፍ ስለፈጸመች+

      ጠፍ ምድረ በዳ ትሆናለች።+

  • አሞጽ 1:11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 11 ይሖዋ እንዲህ ይላል፦

      ‘ስለ ሦስቱ የኤዶም ዓመፅ+ ብሎም ስለ አራቱ እጄን አልመልስም፤

      ምክንያቱም የገዛ ወንድሙን በሰይፍ አሳዷል፤+

      ምሕረት ለማሳየትም እንቢተኛ ሆኗል፤

      በቁጣው ያላንዳች ፋታ ይዘነጣጥላቸዋል፤

      አሁንም ቢሆን በእነሱ ላይ ቁጣው አልበረደም።+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ