ዘፀአት 12:51 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 51 በዚሁ ቀን ይሖዋ እስራኤላውያንን ከነሠራዊታቸው ከግብፅ ምድር አወጣቸው። ዘዳግም 4:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እናንተን ግን ልክ እንደ ዛሬው ሁሉ ይሖዋ የእሱ የግል ንብረት*+ እንድትሆኑ የብረት ማቅለጫ ምድጃ ከሆነችው ከግብፅ አውጥቶ አመጣችሁ።