9 የጽዮን ሴት ልጅ ሆይ፣ እጅግ ሐሴት አድርጊ።
የኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ሆይ፣ በድል አድራጊነት ጩኺ።
እነሆ፣ ንጉሥሽ ወደ አንቺ ይመጣል።+
እሱ ጻድቅ ነው፤ መዳንንም ያመጣል፤
ትሑት ነው፤+ ደግሞም በአህያ፣
በአህያዪቱ ልጅ፣ በውርንጭላ ላይ ይቀመጣል።+
10 የጦር ሠረገላውን ከኤፍሬም፣
ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም እወስዳለሁ።
የጦርነቱ ቀስት ይወሰዳል።
እሱም ለብሔራት ሰላምን ያውጃል፤+
ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር
እንዲሁም ከወንዙ እስከ ምድር ዳርቻ ይሆናል።+