ኢሳይያስ 10:12 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 12 “ይሖዋ በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም የሚያከናውነውን ሥራ ሁሉ ሲያጠናቅቅ በእብሪተኛ ልቡ፣ በኩራቱና በትዕቢተኛ ዓይኑ የተነሳ የአሦርን ንጉሥ ይቀጣዋል።*+ ናሆም 3:7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 7 አንቺን የሚያይ ሁሉ ከአንቺ ይሸሻል፤+ደግሞም ‘ነነዌ ወድማለች! የሚያዝንላት ማን ነው?’ ይላል። አንቺን የሚያጽናና ከየት ማግኘት እችላለሁ? ሶፎንያስ 2:13 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 እሱ እጁን ወደ ሰሜን ይዘረጋል፤ አሦርንም ያጠፋል፤ነነዌንም ባድማና እንደ በረሃ ደረቅ ያደርጋታል።+