ዘዳግም 28:28, 29 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 28 ይሖዋ በእብደት፣ በዕውርነትና+ በግራ መጋባት ይመታሃል። 29 ጨለማ የዋጠው ዓይነ ስውር በዳበሳ እንደሚሄድ ሁሉ አንተም በእኩለ ቀን በዳበሳ ትሄዳለህ፤+ የምታደርገው ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ እንዲሁም ትዘረፋለህ፤ የሚያስጥልህም የለም።+ ኢሳይያስ 59:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+ 10 ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን።+ በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን።
28 ይሖዋ በእብደት፣ በዕውርነትና+ በግራ መጋባት ይመታሃል። 29 ጨለማ የዋጠው ዓይነ ስውር በዳበሳ እንደሚሄድ ሁሉ አንተም በእኩለ ቀን በዳበሳ ትሄዳለህ፤+ የምታደርገው ነገር ሁሉ አይሳካልህም፤ ሁልጊዜ ትጭበረበራለህ፤ እንዲሁም ትዘረፋለህ፤ የሚያስጥልህም የለም።+
9 ከዚህ የተነሳ ፍትሕ ከእኛ ራቀ፤ጽድቅም ወደ እኛ አይደርስም። ብርሃን ይሆናል ብለን በተስፋ ተጠባበቅን፤ ሆኖም ጨለማ ሆነ፤ጸዳልን ተጠባበቅን፤ ሆኖም በጨለማ እንመላለሳለን።+ 10 ልክ እንደ ዓይነ ስውራን ቅጥሩን እየዳበስን እንሄዳለን፤ዓይን እንደሌላቸው ሰዎች እንደናበራለን።+ በምሽት ጨለማ እንደሚሆነው በቀትር ብርሃን እንሰናከላለን፤በብርቱ ሰዎች መካከል እንደ ሙታን ነን።