-
ሕዝቅኤል 22:25, 26አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
25 ነቢያቷ ያደነውን እንስሳ እንደሚቦጫጭቅ የሚያገሳ አንበሳ+ በውስጧ ሴራ ጠንስሰዋል።+ ሰዎችን* ይውጣሉ። ውድ ሀብትንና የከበሩ ነገሮችን ይነጥቃሉ። በውስጧ ያሉትን ብዙ ሴቶች መበለት አድርገዋል። 26 ካህናቷ ሕጌን ጥሰዋል፤+ ቅዱስ ስፍራዎቼንም ያረክሳሉ።+ ቅዱስ በሆነውና ተራ በሆነው ነገር መካከል ምንም ልዩነት አያደርጉም፤+ ደግሞም ንጹሕ ባልሆነውና ንጹሕ በሆነው ነገር መካከል ያለውን ልዩነት አያስታውቁም፤+ ሰንበቶቼንም ለማክበር አሻፈረኝ ይላሉ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስኩ።
-