ኤርምያስ 7:5-7 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’” ኤርምያስ 25:5, 6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ። 6 በእጃችሁ ሥራ ታስቆጡኝ ዘንድ ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፣ አታገልግሏቸው፣ አትስገዱላቸውም፤ አለዚያ ጥፋት አመጣባችኋለሁ።’
5 በእርግጥ መንገዳችሁንና ተግባራችሁን ብታስተካክሉ፣ በሰውና በባልንጀራው መካከል ፍትሕ ብታሰፍኑ፣+ 6 ከባዕድ አገር የመጣውን ሰው፣ ወላጅ አልባ የሆኑ ልጆችንና* መበለቶችን ባትጨቁኑ፣+ በዚህ ቦታ የንጹሕ ሰው ደም ባታፈሱ እንዲሁም ጉዳት ላይ የሚጥሏችሁን ሌሎች አማልክት ባትከተሉ፣+ 7 በዚህች ስፍራ፣ ለአባቶቻችሁ በሰጠኋቸው በዚህ ምድር ለዘለቄታው እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ።”’”
5 እነሱም እንዲህ ይላሉ፦ ‘እባካችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከክፉ መንገዳችሁና ከክፉ ድርጊታችሁ ተመለሱ፤+ ይህን ካደረጋችሁ ይሖዋ ለብዙ ዘመን እንድትኖሩባት ሲል ከረጅም ጊዜ በፊት ለእናንተና ለአባቶቻችሁ በሰጣት ምድር ላይ ትኖራላችሁ። 6 በእጃችሁ ሥራ ታስቆጡኝ ዘንድ ሌሎች አማልክትን አትከተሉ፣ አታገልግሏቸው፣ አትስገዱላቸውም፤ አለዚያ ጥፋት አመጣባችኋለሁ።’