ዘዳግም 30:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ+ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል።+ መዝሙር 147:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ከዚህ ይልቅ ይሖዋ እሱን በሚፈሩ፣ታማኝ ፍቅሩን በሚጠባበቁ ሰዎች ይደሰታል።+ ኢሳይያስ 62:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 በይሖዋ እጅ የውበት ዘውድ፣በአምላክሽ መዳፍ የንጉሥ ጥምጥም ትሆኛለሽ። ኢሳይያስ 65:19 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 19 እኔም በኢየሩሳሌም ደስ እሰኛለሁ፤ በሕዝቤም ሐሴት አደርጋለሁ፤+ከዚህ በኋላ በውስጧ የለቅሶ ድምፅም ሆነ የጭንቅ ጩኸት አይሰማም።”+ ኤርምያስ 32:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ለእነሱ መልካም በማድረግ እጅግ ደስ እሰኛለሁ፤+ በሙሉ ልቤና በሙሉ ነፍሴም* በዚህች ምድር ላይ አጽንቼ እተክላቸዋለሁ።’”+
9 አምላክህ ይሖዋ በአባቶችህ ደስ እንደተሰኘ+ ሁሉ ይሖዋ አንተንም በማበልጸግ ስለሚደሰት የሆድህን ፍሬ፣ እንስሶችህንና የምድርህን ፍሬ በማብዛት በእጅህ ሥራ ሁሉ እጅግ እንድትበለጽግ ያደርግሃል።+