2 “የሰው ልጅ ሆይ፣ የጢሮስን ገዢ እንዲህ በለው፦ ‘ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦
“ልብህ ከመታበዩ የተነሳ+ ‘እኔ አምላክ ነኝ።
በባሕሩ መካከል በአምላክ ዙፋን ላይ እቀመጣለሁ’ ትላለህ።+
በልብህ አምላክ እንደሆንክ የምታስብ ቢሆንም
አንተ ሰው እንጂ አምላክ አይደለህም።
3 እነሆ፣ አንተ ከዳንኤል+ ይበልጥ ጥበበኛ እንደሆንክ ይሰማሃል።
ከአንተ የተሰወረ ሚስጥር እንደሌለ አድርገህ ታስባለህ።