የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ኢሳይያስ 33:20
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 20 በዓሎቻችንን+ የምናከብርባትን ከተማ ጽዮንን ተመልከት!

      ጸጥታ የሰፈነባት መኖሪያ፣

      የማትነቃነቅ ድንኳን+ የሆነችውን ኢየሩሳሌምን ዓይኖችህ ያያሉ።

      የድንኳን ካስማዎቿ ፈጽሞ አይነቀሉም፤

      ከገመዶቿም አንዱ እንኳ አይበጠስም።

  • ኤርምያስ 31:24
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 24 በእሷም ውስጥ ይሁዳና ከተሞቹ ሁሉ እንዲሁም ገበሬዎችና የመንጋ እረኞች በአንድነት ይኖራሉ።+

  • ኤርምያስ 33:10, 11
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 10 “ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሰውም ሆነ ከብት የማይኖርበት ጠፍ መሬት በምትሉት በዚህ ቦታ እንዲሁም ሰው ወይም ነዋሪ ወይም ከብት በሌለባቸው ወና የሆኑ የይሁዳ ከተሞችና የኢየሩሳሌም ጎዳናዎች እንደገና ድምፅ ይሰማል፤ 11 አዎ፣ የሐሴት ድምፅ፣ የደስታ ድምፅ፣+ የሙሽራና የሙሽሪት ድምፅ እንዲሁም “ይሖዋ ጥሩ ስለሆነ+ የሠራዊት ጌታ ይሖዋን አመስግኑ፤ ታማኝ ፍቅሩ ለዘላለም ጸንቶ ይኖራል!”+ የሚሉ ሰዎች ድምፅ ይሰማል።’

      “‘ቀድሞ እንደነበረው ከምድሪቱ ተማርከው የተወሰዱትን ስለምመልስ ወደ ይሖዋ ቤት የምሥጋና መባዎች ይዘው ይመጣሉ’+ ይላል ይሖዋ።”

  • ዘካርያስ 8:4, 5
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 4 “የሠራዊት ጌታ ይሖዋ እንዲህ ይላል፦ ‘ሽማግሌዎችና አሮጊቶች በኢየሩሳሌም አደባባዮች እንደገና ይቀመጣሉ፤ እያንዳንዳቸውም ከዕድሜያቸው ርዝመት የተነሳ* በእጃቸው ምርኩዝ ይይዛሉ።+ 5 የከተማዋም አደባባዮች በዚያ በሚጫወቱ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ይሞላሉ።’”+

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ