41 በሰባተኛው ወር፣ ከንጉሣውያን ቤተሰብ የሆነውና ከንጉሡ ባለሥልጣናት አንዱ የነበረው የኤሊሻማ ልጅ፣ የነታንያህ ልጅ እስማኤል+ ከሌሎች አሥር ሰዎች ጋር ሆኖ በምጽጳ+ ወዳለው ወደ አኪቃም ልጅ ወደ ጎዶልያስ መጣ። በምጽጳ አንድ ላይ ምግብ እየበሉ ሳለ 2 የነታንያህ ልጅ እስማኤልና ከእሱ ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነስተው የሳፋንን ልጅ፣ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መተው ገደሉት። በዚህ መንገድ እስማኤል የባቢሎን ንጉሥ በምድሪቱ ላይ የሾመውን ሰው ገደለው።