-
ሉቃስ 11:9-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 ስለዚህ እላችኋለሁ፣ ደጋግማችሁ ለምኑ፣+ ይሰጣችኋል፤ ሳታሰልሱ ፈልጉ፣ ታገኛላችሁ፤ ደጋግማችሁ አንኳኩ፣ ይከፈትላችኋል።+ 10 ምክንያቱም የሚለምን ሁሉ ይሰጠዋል፤+ የሚፈልግ ሁሉ ያገኛል፤ የሚያንኳኳም ሁሉ ይከፈትለታል። 11 ደግሞስ ከመካከላችሁ ልጁ ዓሣ ቢለምነው በዓሣ ፋንታ እባብ የሚሰጥ አባት ይኖራል?+ 12 ወይስ እንቁላል ቢለምነው ጊንጥ ይሰጠዋል? 13 ታዲያ እናንተ ክፉዎች ሆናችሁ ሳለ ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባትማ ለሚለምኑት መንፈስ ቅዱስን እንዴት አብልጦ አይሰጣቸው!”+
-