-
ማርቆስ 4:37-41አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
37 በዚህ ጊዜ እጅግ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ተነሳ፤ ማዕበሉም ከጀልባዋ ጋር እየተላተመ ወደ ውስጥ ይገባ ጀመር፤ ከዚህም የተነሳ ጀልባዋ በውኃ ልትሞላ ተቃረበች።+ 38 ኢየሱስ ግን በጀልባዋ የኋለኛ ክፍል ትራስ* ተንተርሶ ተኝቶ ነበር። ስለዚህ ቀስቅሰውት “መምህር፣ ስናልቅ ዝም ብለህ ታያለህ?” አሉት። 39 በዚህ ጊዜ ተነስቶ ነፋሱን ገሠጸው፤ ባሕሩንም “ጸጥ በል! ረጭ በል!” አለው።+ ነፋሱ ቆመ፤ ታላቅ ጸጥታም ሰፈነ። 40 ከዚያም “ለምን ትሸበራላችሁ?* አሁንም እምነት የላችሁም?” አላቸው። 41 እነሱ ግን በታላቅ ፍርሃት ተውጠው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ባሕር እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+
-
-
ሉቃስ 8:23-25አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
23 እየተጓዙም ሳሉ ኢየሱስ እንቅልፍ ወሰደው። በዚህ ጊዜ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በሐይቁ ላይ ተነሳ፤ ጀልባቸውም በውኃ መሞላት ስለጀመረች አደጋ ላይ ወደቁ።+ 24 ስለዚህ ሄደው ቀሰቀሱትና “መምህር፣ መምህር ማለቃችን እኮ ነው!” አሉት። እሱም ከእንቅልፉ ነቅቶ ነፋሱንና የሚናወጠውን ውኃ ገሠጸ፤ በዚህ ጊዜ ነፋሱ ቆመ፤ ጸጥታም ሰፈነ።+ 25 ከዚያም “እምነታችሁ የት አለ?” አላቸው። እነሱ ግን በፍርሃት ተውጠውና በጣም ተደንቀው እርስ በርሳቸው “ለመሆኑ ይህ ማን ነው? ነፋስና ውኃ እንኳ ይታዘዙለታል” ተባባሉ።+
-