ማቴዎስ 25:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ንጉሡም መልሶ ‘እውነት እላችኋለሁ፣ ከሁሉ ከሚያንሱት ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ ያደረጋችሁት ሁሉ ለእኔ እንዳደረጋችሁት ይቆጠራል’ ይላቸዋል።+ ማርቆስ 9:41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 41 ደግሞም የክርስቶስ በመሆናችሁ ምክንያት አንድ ጽዋ የሚጠጣ ውኃ የሚሰጣችሁ ሁሉ፣+ እውነት እላችኋለሁ፣ በምንም መንገድ ብድራቱን አያጣም።+ ዕብራውያን 6:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 አምላክ ቅዱሳንን በማገልገልም* ሆነ ወደፊትም ማገልገላችሁን በመቀጠል የምታከናውኑትን ሥራ እንዲሁም ለስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር+ በመርሳት ፍትሕ አያዛባም።