-
ሉቃስ 11:29-32አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
29 ብዙ ሕዝብ በተሰበሰበ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትም ማየት ይፈልጋል፤ ሆኖም ከዮናስ ምልክት በስተቀር ምንም ምልክት አይሰጠውም።+ 30 ምክንያቱም ዮናስ+ ለነነዌ ሰዎች ምልክት እንደሆነ ሁሉ የሰው ልጅም ለዚህ ትውልድ ምልክት ይሆናል። 31 የደቡብ ንግሥት+ የሰለሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ ስለመጣች በፍርድ ወቅት ከዚህ ትውልድ ሰዎች ጋር ተነስታ ትኮንናቸዋለች። ነገር ግን ከሰለሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።+ 32 የነነዌ ሰዎች የዮናስን ስብከት ሰምተው ንስሐ ስለገቡ በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይኮንኑታል።+ ነገር ግን ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ።
-