-
ማቴዎስ 15:9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
9 የሚያስተምሩት የሰውን ሥርዓት ስለሆነ እኔን የሚያመልኩት በከንቱ ነው።’”+
-
-
ማርቆስ 7:8-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
8 የአምላክን ትእዛዝ ትታችሁ የሰውን ወግ አጥብቃችሁ ትከተላላችሁ።”+
9 ደግሞም እንዲህ አላቸው፦ “የራሳችሁን ወግ ለመጠበቅ ስትሉ የአምላክን ትእዛዝ በዘዴ ገሸሽ ታደርጋላችሁ።+ 10 ለምሳሌ ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር’+ እንዲሁም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ* ይገደል’+ ብሏል። 11 እናንተ ግን እንዲህ ትላላችሁ፦ ‘አንድ ሰው አባቱን ወይም እናቱን “እናንተን መጦር የምችልበት፣ ያለኝ ነገር ሁሉ ቁርባን (ማለትም ለአምላክ የተወሰነ ስጦታ) ነው” ቢል’ 12 ከዚያ በኋላ ለአባቱ ወይም ለእናቱ ምንም ነገር እንዲያደርግ አትፈቅዱለትም።+ 13 በመሆኑም ለሌሎች በምታስተላልፉት ወግ የአምላክን ቃል ትሽራላችሁ።+ እንዲህ ያለም ብዙ ነገር ታደርጋላችሁ።”+
-