-
ማርቆስ 7:18-23አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
18 እሱም እንዲህ አላቸው፦ “እናንተም እንደ እነሱ ማስተዋል ተሳናችሁ? ከውጭ ወደ ውስጥ ገብቶ ሰውን ሊያረክስ የሚችል ምንም ነገር እንደሌለ አታውቁም? 19 ምክንያቱም የሚገባው ወደ ልቡ ሳይሆን ወደ ሆዱ ነው፤ ከዚያም ወጥቶ ወደ ጉድጓድ ይገባል።” እንዲህ በማለት ምግብ ሁሉ ንጹሕ መሆኑን አመለከተ። 20 አክሎም እንዲህ አለ፦ “ሰውን የሚያረክሰው ከውስጡ የሚወጣው ነው።+ 21 ከውስጥ ይኸውም ከሰው ልብ+ ክፉ ሐሳብ ይወጣል፦ የፆታ ብልግና፣* ሌብነት፣ ግድያ፣ 22 ምንዝር፣ መጎምጀት፣ ክፋት፣ ማታለል፣ ማንአለብኝነት፣* ምቀኝነት፣* ስድብ፣ ትዕቢትና ሞኝነት። 23 እነዚህ ክፉ ነገሮች ሁሉ ከሰው ልብ ይወጣሉ፤ ሰውንም ያረክሳሉ።”
-