-
ሉቃስ 15:3-7አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
3 በዚህ ጊዜ የሚከተለውን ምሳሌ ነገራቸው፦ 4 “ከእናንተ መካከል 100 በጎች ያሉት ሰው አንዷ ብትጠፋበት 99ኙን በምድረ በዳ ትቶ የጠፋችውን እስኪያገኝ ድረስ አይፈልግም?+ 5 በሚያገኛትም ጊዜ ደስ ብሎት በጫንቃው ላይ ይሸከማታል። 6 ቤት ሲደርስም ጓደኞቹንና ጎረቤቶቹን በአንድነት ጠርቶ ‘የጠፋችውን በጌን ስላገኘኋት የደስታዬ ተካፋዮች ሁኑ’ ይላቸዋል።+ 7 እላችኋለሁ፣ ልክ እንደዚሁ ንስሐ መግባት ከማያስፈልጋቸው 99 ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ታላቅ ደስታ ይሆናል።+
-