-
ማርቆስ 10:41-45አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
41 የቀሩት አሥሩ ይህን ሲሰሙ በያዕቆብና በዮሐንስ ላይ ተቆጡ።+ 42 ሆኖም ኢየሱስ ወደ እሱ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “ብሔራትን የሚገዙ* ነገሥታት በሕዝባቸው ላይ ሥልጣናቸውን እንደሚያሳዩ፣ ታላላቆቻቸውም በኃይል እንደሚገዟቸው ታውቃላችሁ።+ 43 በእናንተ መካከል ግን እንዲህ መሆን የለበትም፤ ከመካከላችሁ ታላቅ መሆን የሚፈልግ ሁሉ አገልጋያችሁ ሊሆን ይገባል፤+ 44 እንዲሁም ከመካከላችሁ ፊተኛ መሆን የሚፈልግ ሁሉ፣ የሁሉ ባሪያ ሊሆን ይገባል። 45 ምክንያቱም የሰው ልጅ እንኳ የመጣው ለማገልገልና+ በብዙ ሰዎች ምትክ ሕይወቱን* ቤዛ አድርጎ ለመስጠት+ እንጂ እንዲገለገል አይደለም።”
-