49 ስለዚህ የአምላክ ጥበብ እንዲህ አለች፦ ‘ነቢያትንና ሐዋርያትን ወደ እነሱ እልካለሁ፤ እነሱም አንዳንዶቹን ይገድላሉ በአንዳንዶቹም ላይ ስደት ያደርሳሉ፤ 50 በመሆኑም ይህ ትውልድ ዓለም ከተመሠረተበት ጊዜ ጀምሮ ለፈሰሰው የነቢያት ደም ሁሉ ተጠያቂ ነው፤+ 51 ከአቤል+ አንስቶ በመሠዊያውና በቤቱ መካከል እስከተገደለው እስከ ዘካርያስ+ ድረስ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂ ነው።’ አዎ፣ እላችኋለሁ፣ ይህ ትውልድ ይጠየቅበታል።