ኢሳይያስ 42:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 42 እነሆ፣ ደግፌ የያዝኩት፣ ደስ የምሰኝበትና*+ የመረጥኩት+ አገልጋዬ!+ መንፈሴን በእሱ ላይ አድርጌአለሁ፤+እሱ ለብሔራት ፍትሕን ያመጣል።+ ማቴዎስ 17:5 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 5 ገና እየተናገረ ሳለም ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ ከደመናውም “በጣም የምደሰትበት፣ የምወደው ልጄ ይህ ነው።+ እሱን ስሙት”+ የሚል ድምፅ ተሰማ። ሉቃስ 3:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 መንፈስ ቅዱስም አካላዊ ቅርጽ ይዞ በርግብ መልክ በእሱ ላይ ወረደ፤ ከዚያም “አንተ የምወድህ ልጄ ነህ፤ በአንተ ደስ ይለኛል” የሚል ድምፅ ከሰማይ መጣ።+