መዝሙር 22:1 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?+ እኔን ከማዳን፣ ከደረሰብኝም ሥቃይ የተነሳ የማሰማውን ጩኸት+ ከመስማትየራቅከው ለምንድን ነው? ኢሳይያስ 53:10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 10 ይሁንና እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር፤* ለሕመም እንዲዳረግም ፈቅዷል። ሕይወቱን* የበደል መባ አድርገህ የምታቀርበው ከሆነ+ዘሩን ያያል፤ ዘመኑን ያስረዝማል፤+እንዲሁም በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር* ይከናወናል።+ ማርቆስ 15:34 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 34 በዘጠነኛውም ሰዓት ኢየሱስ በታላቅ ድምፅ “ኤሊ፣ ኤሊ፣ ላማ ሳባቅታኒ?” ብሎ ጮኸ፤ ትርጉሙም “አምላኬ፣ አምላኬ ለምን ተውከኝ?” ማለት ነው።+
10 ይሁንና እሱን ማድቀቅ የይሖዋ ፈቃድ ነበር፤* ለሕመም እንዲዳረግም ፈቅዷል። ሕይወቱን* የበደል መባ አድርገህ የምታቀርበው ከሆነ+ዘሩን ያያል፤ ዘመኑን ያስረዝማል፤+እንዲሁም በእሱ አማካኝነት ይሖዋ ደስ የሚሰኝበት ነገር* ይከናወናል።+