-
ማቴዎስ 4:1-10አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚህ በኋላ ኢየሱስ፣ ዲያብሎስ+ ይፈትነው+ ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ መራው። 2 እሱም 40 ቀንና 40 ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ። 3 ፈታኙም+ ቀርቦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ እነዚህ ድንጋዮች ዳቦ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው። 4 እሱ ግን “‘ሰው ከይሖዋ* አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰ።+
5 ከዚያም ዲያብሎስ ወደ ቅድስቲቱ ከተማ+ ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ+ 6 እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤ እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ 7 ኢየሱስም “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሎም ተጽፏል” አለው።+
8 እንደገናም ዲያብሎስ በጣም ረጅም ወደሆነ ተራራ ወስዶ የዓለምን መንግሥታት ሁሉና ክብራቸውን አሳየው።+ 9 ከዚያም “አንድ ጊዜ ተደፍተህ ብታመልከኝ እነዚህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው። 10 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “አንተ ሰይጣን፣ ከፊቴ ራቅ! ‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤+ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’+ ተብሎ ተጽፏልና” አለው።
-
-
ሉቃስ 4:1-13አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
4 ከዚያም ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቶ ከዮርዳኖስ ተመለሰ፤ በምድረ በዳም ሳለ መንፈስ ይመራው ነበር፤+ 2 በዚያም 40 ቀን ቆየ፤ ዲያብሎስም ፈተነው።+ በእነዚህም ቀናት ምንም ስላልበላ መጨረሻ ላይ ተራበ። 3 በዚህ ጊዜ ዲያብሎስ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ይህ ድንጋይ ዳቦ እንዲሆን እዘዝ” አለው። 4 ኢየሱስ ግን “‘ሰው በምግብ ብቻ አይኖርም’ ተብሎ ተጽፏል” ሲል መለሰለት።+
5 ዲያብሎስም ወደ አንድ ከፍ ያለ ቦታ አወጣውና የዓለምን መንግሥታት ሁሉ በቅጽበት አሳየው።+ 6 ከዚያም እንዲህ አለው፦ “ይህ ሁሉ ሥልጣንና የእነዚህ መንግሥታት ክብር ተሰጥቶኛል፤+ እኔ ደግሞ ለፈለግኩት መስጠት ስለምችል ለአንተ እሰጥሃለሁ። 7 ስለዚህ አንድ ጊዜ በፊቴ ተደፍተህ ብታመልከኝ ይህ ሁሉ የአንተ ይሆናል።” 8 ኢየሱስም መልሶ “‘ይሖዋ* አምላክህን ብቻ አምልክ፤ ለእሱም ብቻ ቅዱስ አገልግሎት አቅርብ’ ተብሎ ተጽፏል” አለው።+
9 ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ከወሰደው በኋላ በቤተ መቅደሱ አናት* ላይ አቁሞ እንዲህ አለው፦ “የአምላክ ልጅ ከሆንክ እስቲ ራስህን ወደ ታች ወርውር፤+ 10 እንዲህ ተብሎ ተጽፏልና፦ ‘አንተን እንዲጠብቁ መላእክቱን ስለ አንተ ያዛል።’ 11 እንዲሁም ‘እግርህን እንቅፋት እንዳይመታው በእጃቸው ያነሱሃል።’”+ 12 ኢየሱስም መልሶ “‘አምላክህን ይሖዋን* አትፈታተነው’ ተብሏል” አለው።+ 13 ዲያብሎስም ፈተናውን ሁሉ ከጨረሰ በኋላ ሌላ አመቺ ጊዜ እስኪያገኝ ድረስ ትቶት ሄደ።+
-