ማቴዎስ 9:25 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 25 ሕዝቡ ከወጣ በኋላ ወደ ውስጥ ገብቶ እጇን ያዛት፤+ ልጅቷም ተነሳች።+ ሉቃስ 7:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 ከዚያም ቀረብ ብሎ ቃሬዛውን ነካ፤ የተሸከሙት ሰዎችም ባሉበት ቆሙ፤ ኢየሱስም “አንተ ወጣት፣ ተነስ እልሃለሁ!” አለ።+ ሉቃስ 8:54 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 54 እሱ ግን እጇን በመያዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ “አንቺ ልጅ፣ ተነሽ!” አለ።+ የሐዋርያት ሥራ 9:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+
40 ጴጥሮስም ሁሉም እንዲወጡ ካደረገ በኋላ+ ተንበርክኮ ጸለየ። ከዚያም ወደ አስከሬኑ ዞር ብሎ “ጣቢታ፣ ተነሽ!” አለ። እሷም ዓይኖቿን ገለጠች፤ ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ቀና ብላ ተቀመጠች።+