-
ማቴዎስ 14:6-12አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
6 ሆኖም የሄሮድስ ልደት+ በተከበረበት ዕለት የሄሮድያዳ ልጅ በግብዣው ላይ በመጨፈር ሄሮድስን እጅግ ደስ አሰኘችው፤+ 7 በመሆኑም የጠየቀችውን ሁሉ ሊሰጣት በመሐላ ቃል ገባላት። 8 ከዚያም እናቷ በሰጠቻት ምክር መሠረት “የመጥምቁ ዮሐንስን ራስ በዚህ ሳህን ስጠኝ” አለችው።+ 9 ንጉሡ ቢያዝንም ስለ መሐላዎቹና አብረውት ይበሉ ስለነበሩት ሲል የዮሐንስ ራስ እንዲሰጣት አዘዘ። 10 ሰው ልኮም የዮሐንስን ራስ በወህኒ ቤት አስቆረጠ። 11 ራሱን በሳህን አምጥተው ለልጅቷ ሰጧት፤ እሷም ለእናቷ ሰጠቻት። 12 በኋላም የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት መጡና አስከሬኑን ወስደው ቀበሩት፤ ከዚያም መጥተው ለኢየሱስ ነገሩት።
-