-
ማቴዎስ 15:32-38አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
32 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ወደ እሱ ጠርቶ “እነዚህ ሰዎች ሦስት ቀን ሙሉ ከእኔ ጋር ስለቆዩና የሚበሉት ስለሌላቸው አዝንላቸዋለሁ።+ እንዲሁ ጦማቸውን ልሰዳቸው አልፈልግም፤ መንገድ ላይ ዝለው ሊወድቁ ይችላሉ” አላቸው።+ 33 ደቀ መዛሙርቱ ግን “በዚህ ገለልተኛ ስፍራ ይህን ሁሉ ሕዝብ ሊያጠግብ የሚችል በቂ ዳቦ ከየት እናገኛለን?” አሉት።+ 34 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ “ስንት ዳቦ አላችሁ?” አላቸው። እነሱም “ሰባት ዳቦና ጥቂት ትናንሽ ዓሣዎች” አሉት። 35 እሱም ሕዝቡ መሬት ላይ እንዲቀመጥ ካዘዘ በኋላ 36 ሰባቱን ዳቦና ዓሣዎቹን ወሰደ፤ ካመሰገነ በኋላም ቆርሶ ለደቀ መዛሙርቱ ሰጣቸው፤ ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ለሕዝቡ ሰጡ።+ 37 ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ ከዚያም የተረፈውን ቁርስራሽ ሰበሰቡ፤ ቁርስራሹም ሰባት ትላልቅ ቅርጫት ሙሉ ሆነ።+ 38 የበሉትም ከሴቶችና ከትናንሽ ልጆች ሌላ 4,000 ወንዶች ነበሩ።
-