የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ማቴዎስ 16:5-12
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
    • 5 ደቀ መዛሙርቱ ወደ ባሕሩ ማዶ ተሻገሩ፤ በዚህ ጊዜ ዳቦ መያዝ ረስተው ነበር።+ 6 ኢየሱስ “ተጠንቀቁ፣ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠበቁ” አላቸው።+ 7 እነሱም እርስ በርሳቸው “ዳቦ ስላልያዝን ይሆናል” ይባባሉ ጀመር። 8 ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ዳቦ ስላልያዝን ነው ብላችሁ ለምን እርስ በርሳችሁ ትነጋገራላችሁ? 9 አሁንም ነጥቡ አልገባችሁም? ወይስ አምስቱ ዳቦ ለ5,000ዎቹ ሰዎች በቅቶ ከዚያ የተረፈውን ምን ያህል ቅርጫት እንደሰበሰባችሁ አታስታውሱም?+ 10 ወይስ ሰባቱ ዳቦ ለ4,000ዎቹ ሰዎች በቅቶ ከዚያ የተረፈውን በትላልቅ ቅርጫት ምን ያህል እንደሰበሰባችሁ ትዝ አይላችሁም?+ 11 ታዲያ የነገርኳችሁ ስለ ዳቦ እንዳልሆነ እንዴት አታስተውሉም? እንግዲህ ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን እርሾ ተጠንቀቁ።”+ 12 በዚህ ጊዜ ተጠንቀቁ ያላቸው ከዳቦ እርሾ ሳይሆን ከፈሪሳውያንና ከሰዱቃውያን ትምህርት እንደሆነ ገባቸው።

አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
ውጣ
ግባ
  • አማርኛ
  • አጋራ
  • የግል ምርጫዎች
  • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
  • የአጠቃቀም ውል
  • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
  • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
  • JW.ORG
  • ግባ
አጋራ