ማቴዎስ 16:16 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 16 ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ፣+ የሕያው አምላክ ልጅ ነህ”+ ብሎ መለሰለት። ሉቃስ 9:20 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 20 እሱም “እናንተስ ስለ እኔ ማንነት ምን ትላላችሁ?” አላቸው። ጴጥሮስም መልሶ “የአምላክ መሲሕ ነህ”* አለው።+ ዮሐንስ 1:40, 41 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 ዮሐንስ የተናገረውን ከሰሙትና ኢየሱስን ከተከተሉት ሁለት ሰዎች አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ+ ነበር። 41 እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሲሑን አገኘነው”+ አለው (መሲሕ ማለት “ክርስቶስ” ማለት ነው)፤ ዮሐንስ 6:68, 69 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 68 ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን?+ አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።+ 69 አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ እንደሆንክ አምነናል፤ ደግሞም አውቀናል።”+
40 ዮሐንስ የተናገረውን ከሰሙትና ኢየሱስን ከተከተሉት ሁለት ሰዎች አንዱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም እንድርያስ+ ነበር። 41 እንድርያስ በመጀመሪያ የራሱን ወንድም ስምዖንን አገኘውና “መሲሑን አገኘነው”+ አለው (መሲሕ ማለት “ክርስቶስ” ማለት ነው)፤
68 ስምዖን ጴጥሮስም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ጌታ ሆይ፣ ወደ ማን እንሄዳለን?+ አንተ የዘላለም ሕይወት ቃል አለህ።+ 69 አንተ የአምላክ ቅዱስ አገልጋይ እንደሆንክ አምነናል፤ ደግሞም አውቀናል።”+