ማቴዎስ 20:22, 23 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 ኢየሱስም መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ በቅርቡ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም “እንችላለን” አሉት። 23 እሱም “በእርግጥ የእኔን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤+ በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” አላቸው።+ ሉቃስ 12:50 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 50 እርግጥ እኔ የምጠመቀው አንድ ጥምቀት አለኝ፤ ይህ እስኪጠናቀቅ ድረስ በጣም ተጨንቄአለሁ!+ ዮሐንስ 18:11 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 11 ይሁን እንጂ ኢየሱስ ጴጥሮስን “ሰይፉን ወደ ሰገባው መልስ።+ አብ የሰጠኝን ጽዋ መጠጣት አይኖርብኝም?” አለው።+ ሮም 6:3 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 3 ወይስ ክርስቶስ ኢየሱስ ውስጥ የተጠመቅን+ ሁላችን እሱ ሞት ውስጥ እንደተጠመቅን+ አታውቁም?
22 ኢየሱስም መልሶ “የምትለምኑትን አታውቁም። እኔ በቅርቡ የምጠጣውን ጽዋ ልትጠጡ ትችላላችሁ?” አላቸው።+ እነሱም “እንችላለን” አሉት። 23 እሱም “በእርግጥ የእኔን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤+ በቀኜ ወይም በግራዬ መቀመጥ ግን አባቴ ላዘጋጀላቸው የሚሰጥ እንጂ በእኔ ፈቃድ የሚሆን አይደለም” አላቸው።+