20 “ይሁንና ኢየሩሳሌም በጦር ሠራዊት ተከባ ስታዩ+ መጥፊያዋ እንደቀረበ እወቁ።+ 21 በዚህ ጊዜ በይሁዳ ያሉ ወደ ተራሮች ይሽሹ፤+ በከተማዋ ውስጥ ያሉም ከዚያ ይውጡ፤ በገጠር ያሉም ወደ እሷ አይግቡ፤ 22 ምክንያቱም የተጻፈው ነገር ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይህ የፍትሕ እርምጃ የሚወሰድበት ጊዜ ነው። 23 በእነዚያ ቀናት ለነፍሰ ጡሮችና ለሚያጠቡ ወዮላቸው!+ ምክንያቱም በምድሪቱ ላይ ታላቅ መከራ፣ በዚህ ሕዝብም ላይ ቁጣ ይመጣል።