ኤርምያስ 31:31 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 31 “እነሆ፣ ከእስራኤል ቤትና ከይሁዳ ቤት ጋር አዲስ ቃል ኪዳን የምገባበት ጊዜ ይመጣል” ይላል ይሖዋ።+ ዕብራውያን 7:22 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 22 እንደዚሁም ኢየሱስ ለተሻለ ቃል ኪዳን ዋስትና* ሆኗል።+ ዕብራውያን 9:15 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 15 የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው።+ መካከለኛ የሆነውም የተጠሩት የዘላለማዊውን ውርሻ+ ተስፋ ይቀበሉ ዘንድ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በሞቱ የተነሳ ሲሆን በእሱ ሞት አማካኝነት በቀድሞው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ሕግ በመተላለፍ ከፈጸሟቸው ድርጊቶች በቤዛ ነፃ ወጥተዋል።+
15 የአዲስ ቃል ኪዳን መካከለኛ የሆነው በዚህ ምክንያት ነው።+ መካከለኛ የሆነውም የተጠሩት የዘላለማዊውን ውርሻ+ ተስፋ ይቀበሉ ዘንድ ነው። ይህ ሁሉ ሊሆን የቻለው በሞቱ የተነሳ ሲሆን በእሱ ሞት አማካኝነት በቀድሞው ቃል ኪዳን ሥር ሆነው ሕግ በመተላለፍ ከፈጸሟቸው ድርጊቶች በቤዛ ነፃ ወጥተዋል።+