ማቴዎስ 27:59, 60 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 59 ከዚያም ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ገነዘው፤+ 60 ከዓለት ፈልፍሎ በሠራው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥም አኖረው።+ ከዚያም አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋውና ሄደ። ሉቃስ 23:53 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 53 አስከሬኑንም አውርዶ+ በበፍታ ገነዘው፤ ከዚያም ማንም ሰው ተቀብሮበት በማያውቅ ከዓለት ተፈልፍሎ በተሠራ መቃብር ውስጥ አኖረው።+ ዮሐንስ 19:40 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 40 የኢየሱስንም አስከሬን ወስደው በአይሁዳውያን የአገናነዝ ልማድ መሠረት ጥሩ መዓዛ ባላቸው በእነዚህ ቅመሞች ተጠቅመው በበፍታ ጨርቅ ገነዙት።+
59 ከዚያም ዮሴፍ አስከሬኑን ወስዶ በንጹሕ በፍታ ገነዘው፤+ 60 ከዓለት ፈልፍሎ በሠራው በራሱ አዲስ መቃብር ውስጥም አኖረው።+ ከዚያም አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባሎ የመቃብሩን ደጃፍ ዘጋውና ሄደ።