-
1 ሳሙኤል 21:1-6አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
21 በኋላም ዳዊት ካህኑ አሂሜሌክ ወደሚገኝበት ወደ ኖብ+ መጣ። አሂሜሌክም ዳዊትን ሲያገኘው ተንቀጠቀጠ፤ እሱም “ምነው ብቻህን? ሰው አብሮህ የለም?” አለው።+ 2 ዳዊትም ለካህኑ ለአሂሜሌክ እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “ንጉሡ አንድ ጉዳይ እንዳስፈጽም አዞኝ ነበር፤ ሆኖም ‘ስለሰጠሁህ ተልእኮና ስላዘዝኩህ ነገር ማንም ሰው ምንም ነገር እንዳያውቅ’ ብሎኛል። ከሰዎቼም ጋር የሆነ ቦታ ላይ ለመገናኘት ተቀጣጥረናል። 3 ስለዚህ አሁን እጅህ ላይ አምስት ዳቦ ካለ ወይም የተገኘውን ማንኛውንም ነገር ስጠኝ።” 4 ካህኑ ግን ዳዊትን እንዲህ አለው፦ “ማንኛውም ሰው የሚበላው ዓይነት ዳቦ የለኝም፤ ሰሞኑን ሰዎቹ ራሳቸውን ከሴት ጠብቀው*+ ከሆነ ግን የተቀደሰው ኅብስት አለ።”+ 5 ስለዚህ ዳዊት ካህኑን እንዲህ አለው፦ “ከዚህ በፊት ለውጊያ እንደወጣሁባቸው ጊዜያት ሁሉ አሁንም ፈጽሞ ሴቶች ወደ እኛ አልቀረቡም።+ ተራ በሆነ ተልእኮም እንኳ የሰዎቹ አካል ቅዱስ ከነበረ ታዲያ ዛሬማ እንዴት ይበልጥ ቅዱስ አይሆን!” 6 በመሆኑም ካህኑ የተቀደሰውን ኅብስት ሰጠው፤+ ምክንያቱም ትኩስ ኅብስት በሚተካበት ቀን ከይሖዋ ፊት ከተነሳው ገጸ ኅብስት በስተቀር ሌላ ዳቦ አልነበረም።
-