ማቴዎስ 9:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ኢየሱስ ከዚያ ተነስቶ እየሄደ ሳለ ማቴዎስ የሚባል ሰው በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየና “ተከታዬ ሁን” አለው። በዚህ ጊዜ ተነስቶ ተከተለው።+ ማርቆስ 2:14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 14 በመንገድ እያለፈ ሳለም የእልፍዮስን ልጅ ሌዊን በቀረጥ መሰብሰቢያው ቦታ ተቀምጦ አየውና “ተከታዬ ሁን” አለው። በዚህ ጊዜ ተነስቶ ተከተለው።+