ዘፀአት 20:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+ ዘዳግም 5:13, 14 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው።+ ዮሐንስ 5:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም* አንስቶ መሄድ ጀመረ። ቀኑም ሰንበት ነበር። 10 በመሆኑም አይሁዳውያን የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት እኮ ነው፤ ምንጣፍህን* እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት።+
9 ሥራህንና የምታከናውናቸውን ነገሮች በሙሉ በስድስት ቀን ሠርተህ አጠናቅ፤+ 10 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው። በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ የቤት እንስሳህም ሆነ በሰፈርህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው ምንም ሥራ አትሥሩ።+
13 ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀን ትሠራለህ፤+ 14 ሰባተኛው ቀን ግን ለአምላክህ ለይሖዋ ሰንበት ነው።+ በዚህ ቀን አንተም ሆንክ ወንድ ልጅህ ወይም ሴት ልጅህ፣ ወንድ ባሪያህም ሆነ ሴት ባሪያህ፣ በሬህም ሆነ አህያህ ወይም ማንኛውም የቤት እንስሳህ አሊያም በከተሞችህ* ውስጥ ያለ የባዕድ አገር ሰው+ ምንም ሥራ አትሥሩ፤+ ይህም አንተ እንደምታርፈው ወንድ ባሪያህና ሴት ባሪያህ እንዲያርፉ ነው።+
9 ሰውየውም ወዲያውኑ ተፈወሰ፤ ምንጣፉንም* አንስቶ መሄድ ጀመረ። ቀኑም ሰንበት ነበር። 10 በመሆኑም አይሁዳውያን የተፈወሰውን ሰው “ሰንበት እኮ ነው፤ ምንጣፍህን* እንድትሸከም ሕጉ አይፈቅድልህም” አሉት።+