-
ዘሌዋውያን 24:5-9አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
-
-
5 “አንተም የላመ ዱቄት ወስደህ የቀለበት ቅርጽ ያላቸው 12 ዳቦዎችን ጋግር። እያንዳንዱ ዳቦ ከሁለት አሥረኛ ኢፍ* ዱቄት የተዘጋጀ መሆን ይኖርበታል። 6 እነዚህንም በይሖዋ ፊት ባለው ከንጹሕ ወርቅ በተሠራው ጠረጴዛ+ ላይ ስድስት ስድስት አድርገህ በማነባበር በሁለት ረድፍ ታስቀምጣቸዋለህ።+ 7 ተነባብሮ በተቀመጠው በእያንዳንዱ ረድፍ ላይም ንጹሕ ነጭ ዕጣን አድርግ፤ ይህም ለምግቡ መታሰቢያ እንዲሆን+ ለይሖዋ በእሳት የሚቀርብ መባ ይሆናል። 8 እሱም በየሰንበቱ ዘወትር በይሖዋ ፊት ይደርድረው።+ ይህ በእኔና በእስራኤላውያን መካከል ያለ ዘላቂ ቃል ኪዳን ነው። 9 ይህም የአሮንና የወንዶች ልጆቹ ይሆናል፤+ ለይሖዋ በእሳት ከሚቀርቡት መባዎች መካከል ለእሱ እጅግ ቅዱስ ነገር ስለሆነ ቅዱስ በሆነ ቦታ ይበሉታል፤+ ይህ ዘላቂ ሥርዓት ነው።”
-